=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ኡለማዎች የአንድን ሰው ኢስላም ዋጋ የሚያሰጡ ብዙ ነገሮች እንዳሉ የጠቀሱ ቢሆንም የሚከተሉት 10 ነገሮች የተለመዱ ናቸው።
1 በአሏህ ላይ ማሻረክ
2 በሰዎች እና በአሏህ መካከል አስታራቂን(ባላንጣን) ማበጀት
3 አሏህን በኢባዳ የሚያሻርኩትን እንደ ከሐዲ አለመቁጠር ፣ ክህደታቸውን መጠራጠር ወይም እምነታቸው ትክክል እንደሆነ ማሰብ
4 ከቁርአን በላይ የሆነ መመሪያ አለ ብሎ ማመን ወይም ሌሎች ድንጋጌዎች(ህጎች) ከቁርአን በላይ ናቸው ብሎ ማመን ለምሳሌ በሰው ዘንድ የተደነገጉ ህጐችን ከኢስላም ህግጋት በላይ መውደድ እና በእነሱ መተዳደር
5 ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ያዘዙትን ማንኛውንም ነገር መጥላት
6 በኢስላም ክፍል በሆነ ነገር ላይ መቀለድ(መሳለቅ): በቅጣቱም ይሁን በምንዳው
7 በድግምት መስራራት
8 ከሃዲዎች በአማኞች ላይ የመሚያደርጉትን ዘመቻ መደገፍ
9 ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ይዘውት የመጡትን የእስልምና ህግጋት ሰዎች መተው ይችላሉ ብሎ ማመን
10 የአሏህ ሃይማኖት ባለመማር ወይም ባለመተግበር ከአሏህ ሃይማኖት መራቅ
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|